ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ለጤናዎ ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉ?

ጥሩ እንቅልፍ ለጤናዎ በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉ? ብዙ ጥቅሞች አሉት። እንዱን ጥቅም ለመጥቀስ ያህል ከተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች (ምሳሌ) የምንረዳው በየእለቱ ጥሩ እንቅልፍ ካላገኘን ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላችን ከፍ እንደሚል ነው።

እና ምን ያህል ሰዓታት በቀን (24 ሰዓት ውስጥ) መተኛት የስፈልጋል?

የአሜሪካ CDC የበሽታዎች መቆጣጠርያ ድርጅት የሚመክረው ይህንን ነው፡

  • እድሜ ከ 0-3 ወር —– በቀን ከ 14-17 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።
  • እድሜ ከ 4–12 ወር —– ባጠቃላይ በቀን ከ 12–16 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።
  • እድሜ ከ 1–2 አመት —– ባጠቃላይ በቀን ከ 11–14 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።
  • እድሜ ከ 3–5 አመት —– ባጠቃላይ በቀን ከ 10–13 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።
  • እድሜ ከ 6–12 አመት —– በቀን ከ 9–12 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።
  • እድሜ ከ 13–18 አመት —– በቀን ከ 8–10 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።
  • እድሜ ከ 18–60 አመት —– በቀን ሲያንስ 7 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።
  • እድሜ ከ 61–64 አመት —– በቀን ከ 7–9 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።
  • እድሜ ከ 65 አመት በላይ —– በቀን ከ 7–8 ሰዓት እንቅልፍ ቢያገኙ ይመከራል።

Photo by William Fortunato from Pexels